Free tender detail

አዲስ ዘመን ቅዳሜ ህዳር 12 ቀን 2013 .      

የጨረታ ማስታወቂያ

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የጨረታ

ማስታወቂያ ቁጥር PPPDS/VP-14FBI/02/03/2013

የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ የውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር፣ የትራንስፖርት ባለስልጣን፣ የአለርት ሆስፒታል፣ የፕሬዚዳንት /ቤት፣ የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት፣ የአካባቢ፣ የደንና የአየር   ንብረት ለውጥ ኮሚሽን፣ የማዕከላዊ ስታቲክስ ኤጀንሲ፣ የብሔራዊ   አክሬዲቴሽን /ቤት፣ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር፣ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ እና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ያገለገሉ 43ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በገንዘብ ሚኒስቴር ቁጥር 2 ግቢ ውስጥ በሚገኘው የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሕንፃ ቁጥር 5 ቢሮ ቁጥር 007 በመምጣት የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
  3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 300 እስከ 1000 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ከላይ በተጠቀሱት /ቤቶች በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
  4. ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ እና የጉምሩክ ቀረጥ ግብር ወጪ ካለው ባለንብረቱ መሥሪያ ቤት የሚሸፍን ሲሆን የስም ማዛወሪያ፣ የትራንዚትእናሌሎች ወጪዎች ግን በገዥው ይሸፈናል፣
  5. ተጫራቾች የሚገዙትን ተሽከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨ ረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋ ገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው   ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል። የተሽከርካሪውን የመነሻ ዋጋ20 በመቶ (20%) ያላስያዘ እናበሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣
  6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ምሮ 20 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4 15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት እያስተጓጉልም፣
  7. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው 7 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መከፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መከፈል ካልቻሉ ያስያዙት   የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል።
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሽነፈባቸውን ተሽከርካሪዎች ሙሉ ክፍያ ከፍሎ እስከሚወስድ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ   በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
  9. አገልግሎቱ ያወጣውን ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመከፈል ተሽከርካሪውን 10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው
  11. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ስልክ ቁጥር፡- 011-154-04-25  ወይም 011-122 37-08/36 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
  12. አገልግሎቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

የመንግሥት ግዥና ንብረት

ማስወገድ አገልግሎት

አዲስ አበባ




___________________________________________________________________________________
Category : Sale., Vehicle and Spare Parts, Vehicle Sale
Posted Date : 2020-11-23 04:12:20
Deadline :
2020-12-10 (Bid Closed.)

 
   

Copyright © 2011 - 2024 Habesha Tender
Telephone: +251-118-961881/ +251-911-891169 / +251-920-105191, P.O.Box: 122841
Office Address: Aberus Complex 4th floor, office No 405, Bole Road infront of Dembel City Center
Email: contact@habeshatender.com || Website: www.habeshatender.com