Free tender detail

አዲስ ዘመን ሐሙስ ታህሳስ 22 ቀን 2013 .      

የጨረታ ማስታወቂያ

ብግጨ 27/2013

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከመንግስት በተመደበለት በጀች ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የፌሮ ብረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ዕቃውን ለማቅረብ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማቅረብ የሚችሉ
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 / ሃምሳ ሺህ / ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሠርተው ማቅረብ ሲኖርባቸው በጥቃቅን የተደራጁ ከአደራጃቸው የመንግስት /ቤት የዋስትና ደብዳቤ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም በማሠራት- ማቅረብ አለባቸው፣
  3. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀለት 7/ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ 8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት፣
  4. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች የጨረታ ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 እና አዲስ አበባ አራት ኪሎ ከቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ሮሚና ካፌ ህንፃ 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በመቅረብ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ / በመክፈል ለነዱን መግዛት ይችላሉ
  5. ተወዳዳሪ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 359 ድረስ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 30 ድረስ በመቅረብ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  6. ጨረታው 16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡ዐዐ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4 30 በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቶች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታን ጨምሮ ጨረታው በእለቱ ይከፈታል።
  7. የጨረታውን ፋይናንሽያል ኦርጅናል ዶክመንቶች እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ የታሸገ ፖስታ የማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የመ/ቤቱን ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ አንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ሲኖርባቸው ፋይናንሽያል ዶክመንቶች ከኦርጅናሉ በተጨማሪ አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
  8.  ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ:- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-771-66-91 ደብረ ማርቆስ መጠየቅ ያችላሉ።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

 




___________________________________________________________________________________
Category : Purchase., Steel/ Metals and Aluminium, Steels/ Irons and Metals
Posted Date : 2021-01-01 04:30:33
Deadline :
2021-01-15 (Bid Closed.)

 
   

Copyright © 2011 - 2024 Habesha Tender
Telephone: +251-118-961881/ +251-911-891169 / +251-920-105191, P.O.Box: 122841
Office Address: Aberus Complex 4th floor, office No 405, Bole Road infront of Dembel City Center
Email: contact@habeshatender.com || Website: www.habeshatender.com