Free tender detail

አዲስ ዘመን አርብ መስከረም 7 ቀን 2013 .      

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን እቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የእቃ/ የአገልግሎት ግዥ

  • ሎት1. የሕትመት ዥዎች
    • 1.1. የአጀንዳ ሕትመት
    • 1.2. የጠረጴዛ ካላንደር ህትመት ግዥ
    • 1.3. የመፅሄት ህትመት

ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች በማሟላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ 2013 . ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬ ያላቸው፣ የገቢዎች ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ከመንግስት ግዥ ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች ለሎት አንድ (01) የጨረታ ማስከበሪያ 5,000.00 / አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  4. ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ለሎት አንድ (01) ብር 100.00 ( አንድ መቶ ብር) በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ንዑስ የሥራ ሂደት ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለፅና መሆን አለበት፡፡ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት።
  7. ጨረታውን በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል፡፡
  8. ድርጅቱ የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል።
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21/01/2014 ዓም ከሰዓት 8 00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስባት ይችላሉ፣ ጨረታው ከሰዓት በዕለቱ 8 30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የግዥ ዓይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ (ወይም ናሙና ለሚያስፈልገው) እና ፋይናንሽያል በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ Bid document/ መሰረት ጨረታው ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናንሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባት አለባቸው።
  11. የጨረታ ሂደቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሰረት ጨረታው ሰነዳችሁ የሚገመም ሲሆን ለእያንዳንዳቸው ናሙና መረጣ ያላለፈ ተጫራች ፋይናንሻል ሰነድ ሳይከፈት ውድቅ ይሆናል፡፡ የጨረታ ሰነዳችሁ ስታስገቡ ናሙና ማቅረብ ግዴታ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 011 55191 00/0115 53 07 67/011 5 15 73 37

የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት




___________________________________________________________________________________
Category : Printing and Publishing., Printing and Publishing Service, Purchase.
Posted Date : 2021-09-18 02:23:29
Deadline :
2021-10-01 (Bid Closed.)

 
   

Copyright © 2011 - 2024 Habesha Tender
Telephone: +251-118-961881/ +251-911-891169 / +251-920-105191, P.O.Box: 122841
Office Address: Aberus Complex 4th floor, office No 405, Bole Road infront of Dembel City Center
Email: contact@habeshatender.com || Website: www.habeshatender.com