Free tender detail

አዲስ ዘመን ማክሰኞ መስከረም 11 ቀን 2013 .      

የኮንስትራክሽን እቃዎች ግዥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አኮ/ /13/21

ዓባይ ኮንስትራክሽን /የተ/የግ/ማህበር ለተለያዩ የመስኖና መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ

  • የተለያዩ የኮንስትራክሽን እቃዎች ( የአርማታ ብረት ሲሚንቶ ፎርም ወርከ ጣውላ ሚስማር እና ሌሎችንም) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
  3. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5.  የዕቃውን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ ብር ብቻ) በመከፈል / ዳር ከተማ ቀበሌ-14 ከቻይና ካምፕ ፊት ለፊት ዓባይ ኮንስትራክሽን /የተ/የግ/ማህበር ከግዥ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ::
  7.  ተጫራቾች ለሚወዳደሩ በት 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CP O) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) በዓባይ ኮንስትራክሽን /የተ/የግ/ማህበር ስም በማሰራት ማስያዝ አለባቸው
  8.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ለኮንስትራክሽን እቃዎች ግዥ የወጣ ግልፅ ጨረታ ተብሎ ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት እስከ 15 ኛው ቀን 8 00 በስራ ሰዓት ( ቅዳሜ እስከ 5 30 ጨምሮ) ከዋናው / ቤት / ዳር ከተማ ቀበሌ-14 ከቻይና ካምፕ ፊትለፊት ዓባይ ኮንስትራክሽን / የተ/ የግ/ ማህበር ግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9.  ጨረታው ከወጣበት ጀምሮ 15 ኛው ቀን 8 00 ሰዓት የሚታሸግ ሆኖ 15 ኛው ቀን የበዓላት ቀን ወይም እሁድና ቅዳሜ ከሆነ ግን በሚቀጥለው የስራ ቀን ከቀኑ 8 00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 30 ደቂቃ በኋላ ከቀኑ 8 30 ተጫራቾች ወይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058- 320 04 14/058-320 34 94 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ዓባይ ኮንስትራክሽን / የተ/ የግ/ ማህበር




___________________________________________________________________________________
Category : Building Materials, Construction and Construction Machinery, Construction Raw Materials, Purchase.
Posted Date : 2021-09-22 06:17:33
Deadline :
2021-10-05 (Bid Closed.)

 
   

Copyright © 2011 - 2024 Habesha Tender
Telephone: +251-118-961881/ +251-911-891169 / +251-920-105191, P.O.Box: 122841
Office Address: Aberus Complex 4th floor, office No 405, Bole Road infront of Dembel City Center
Email: contact@habeshatender.com || Website: www.habeshatender.com