Free tender detail

አዲስ ዘመን ሰኞ ህዳር 6 ቀን 2013 .      

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሰት መስተዳድር በሰሜን ሸዋ ዞን የአለልቱ ወረዳ አስተዳደር /ቤት ለወረዳ /ቤቶች

  • ባለ ሶስት ወለል ህንፃ (G+3 ) ቢሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ መስራት ለሚችል እስከ 5 ደረጃ ብቻ ያሉትን የግንባታ ኮንትራክትሮች እና አጠቃላይ ኮንትራክትሮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

የተጫራቾች መመሪያ፡-

  1. ከኢፊዲሪ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተሰጠ የግንባታ ህጋዊ ፈቃድ እና ከሚመለከተዉ አካል የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና ከኦሮሚያ ገቢዎች ባለስልጣን ወይም ከኢፊዲሪ ገቢዎች ባለስጣን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ,
  3. የንግድ ፈቃዳቸውን ያደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) ማቅረብ የሚችሉ፤እና የተጨማሪ እሴትታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፡
  4. የጨረታው ማስከበሪያ /ቢድ ቦን / ብር 100,000/ አንድ መቶ ) ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል
  5. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይቻልም፡፡
  6. ተጫራቾች የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ከሚመለከተዉ አካል ማቅረብ አለባቸዉ፣
  7. በተሠጠው ስፔሲፊኬሽንና ዲዛይን መሠረት ተሟልተው ካልቀረቡና ማንኛውንም ዓይነት ስህተት ሲፈጽሙ ሃላፊነቱ የኮንትራክተሩ ነው፡፡
  8.  ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዋና እና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበትን የግንባታው ስፔሲፊኬሽን መሰረት በነጠላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር የጠቅላላ ዋጋ ይወሰዳል፡፡
  10. የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማይመለስ ብር 500/ አምስት መቶ ብር በመክፈል ከአለልቱ ወረዳ / / / / ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  11.  የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት 21 የስራ ቀን ቆይቶ 28/3/14 ዓም ከቀኑ 6 ፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት ከቀኑ 8 00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
  12.  ተጫራቾች አሸናፊነታቸው እንደታወቀ ከጽ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማሉ፡፡
  13.  በጨረታው የተሸነፉትም ተሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ ለጨረታ ማስከበሪያ ስዋስትና ያስያዙት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  14. ከዚህ በላይ በተገለጸው መሰረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ሳይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ሲቀሩ ለውል ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘ - ገንዘብ ለጽ/ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  15. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትከከል ጽፈው መፈረም አለባቸው፡፡
  16. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት፡፡
  17. አሸናፊ ኮንትራክተር በጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ ማህበራት የግንባታዉን 40 % የመስጠት ግዴታ አለበት፤
  18. አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት በፍጹም አይቻልም፡፡
  19. ጨረታው 7/3/14 . ጀም 28/3/14 . ቆይቶ 6 00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8 00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ ቤቱ ቢሮ ቁጥር 1 ውስጥ ይከፈታል።
  20.  ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻ ማቆየ ይኖርባቸዋል።

አድራሻ - በደሴ መንገድ በዋናዉ አስፋልት ከኢ. 55 ኪሜ በስተቀኝ 150 ሜትር ገባ ብሎ ነዉ::

በስልክ ቁጥር 0116310305/0209 የአለልቱ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር / ቤት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአለልቱ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር / ቤት

_____________________________________

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚወጡ ሁሉንም የግንባታ ጨረታዎችን እንደወጡ በየቀኑ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ!
 https://t.me/habeshatendercon




___________________________________________________________________________________
Category : Construction and Construction Machinery, House and Building Construction
Posted Date : 2021-11-16 04:11:34
Deadline :
2021-12-07 (Bid Closed.)

 
   

Copyright © 2011 - 2024 Habesha Tender
Telephone: +251-118-961881/ +251-911-891169 / +251-920-105191, P.O.Box: 122841
Office Address: Aberus Complex 4th floor, office No 405, Bole Road infront of Dembel City Center
Email: contact@habeshatender.com || Website: www.habeshatender.com