Free tender detail

አዲስ ዘመን እሁድ ህዳር 18 ቀን 2015 .      

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ኮማንዶና አየር ወለድ / ማዕከል / 002/2015

በሀገር መከላከያ / በኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የኮማንዶና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል በማዕከሉ ውስጥ፡- ቢሮና መፀዳጃ ቤትን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ያካተተ ዘመናዊ አንፊ ቲያትር በመረጠው ዲዛይን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ
  2. የቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችል
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው
  4. ተወዳዳሪ ድርጅት ከደረጃ 3 እስከ 6 ሲሆን ደረጃው ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የተሰጠ መሆኑን ማስረጃ የሚያቀርብ መሆን አለበት፡፡
  5. አሸናፊ ድርጅት አሸናፊ ሆኑ ሲገለፅለት ከማሰልጠኛ ማዕከሉ ጋር ውል በመግባት የግንባታ ዕቃዎችን እራሱ በማቅረብ በፍጥነት ስራውን ማስጀመር የሚችል መሆን አለበት
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 525.000.00/ አምስት መቶ ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በኮማንዶና አየር ወለድ /ማዕከል ስም በባንክ በተመሰከረለት .. ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ብላቴ በሚገኘው በኮማንዶና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕክል ድረስ በመምጣት ማየት ይችላል፡፡
  8. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ አስራ አንደኛው ቀን ከቀኑ 8:30 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8:40 ብላቴ በሚገኘው የኮማንዶና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል ቢሮ ውስጥ በሚገኘው ሚኒ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ አስራ አንደኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል።
  9. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ብላቴ የኮማንዶና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል ግዥ ዴስክ ቢሮ ቁጥር 23 የማይመለስ 100 ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. ማሰልጠኛ ማዕከሉ ጨረታውን የሚገመግመው የቴክኒክ እና የዋጋ ሰነድ ለየብቻ ሲሆን ተጫራቾች የመገምገሚያ ነጥቦቹ የሚይዙትን ክብደት ከጨረታ ሰነድ ላይ በግልፅ ማየት ይችላሉ፡፡
  11. ማሰልጠኛ ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 228 00 33 የውስጥ መስመር 131 ፋክስ ቁጥር 046 228 00 08

የኮማንዶ እና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል




___________________________________________________________________________________
Category : Construction and Construction Machinery, House and Building Construction
Posted Date : 2022-11-28 23:14:23
Deadline :
2022-12-07 (Bid Closed.)

 
   

Copyright © 2011 - 2024 Habesha Tender
Telephone: +251-118-961881/ +251-911-891169 / +251-920-105191, P.O.Box: 122841
Office Address: Aberus Complex 4th floor, office No 405, Bole Road infront of Dembel City Center
Email: contact@habeshatender.com || Website: www.habeshatender.com