Free tender detail

አዲስ ዘመን ቅዳሜ መጋቢት 23 ቀን 2015 ዓ . ም
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ ፍቃዱ ገመቹ እና በፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ተስፋዬ ገመቹ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 2888194 በ7/4/2013 ዓ.ም እና በመ/ቁ 280323 በ22/4/2012 ዓ.ም በ10/8/2014 ዓ.ም እና በ25/9/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 3 የቤ.ቁ 1788 የሆነው መኖሪያ ቤት በመለያ ቁጥር AA00003030/1634 የሆነ የተመዘገበ ካርታ ያለው የተመዘገበ የቦታ ስፋት 380 ካ/ሜ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 755,960 (ሰባት መቶ ሀምሳ አምስት ሺ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 22 ቀን 2015 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል። የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት ¼  ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬቱ የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።
በፌዴራል ፍ/ቤቶች  የፍርድ አፈፃፀም ዳይክቶሬት



___________________________________________________________________________________
Category : Foreclosure., House and Building Foreclosure, House and Building., House and Building Sale, Sale.
Posted Date : 2023-04-03 05:54:30
Deadline :
2023-05-30 (Bid Closed.)

 
   

Copyright © 2011 - 2024 Habesha Tender
Telephone: +251-118-961881/ +251-911-891169 / +251-920-105191, P.O.Box: 122841
Office Address: Aberus Complex 4th floor, office No 405, Bole Road infront of Dembel City Center
Email: contact@habeshatender.com || Website: www.habeshatender.com