Free tender detail

አዲስ ልሳን ቅዳሜ ግንቦት 5 ቀን 2015 .

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ፤ ኮልፌ ቀራንዮ፤ በአራዳ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፤ በየካ፤ በቦሌ፣ በአዲስ ከተማ፣ በለሚ ኩራ፣ በቂርቆስ፣ በጉለሌ፣ እና በልደታ /ከተሞች የሚገኙ

  • ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል.

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

  1. ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000.00 ( አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከግንቦት 10 ቀን 2015 . እስከ ግንቦት 23 ቀን 2015 . ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቢሮ ቁጥር 101 (ለም ሆቴል አከበቢ ኤም ህንፃ ላይ) በመገኘት መግዛት ይችላሉ።
  2. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ማንነቱ የሚገልፅ መታወቂያ ያዞ በአካል መቅረብ ይኖርበታል። በውክልና ከሆነ የተወካይ መታወቂያ እና የውክልና ማስረጃ ያስፈልጋል።
  3. ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ቦታ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎችን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ አለባቹህ።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መስፈርት መሠረት መሆን ይኖርበታል።
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቦታ የመነሻ ጠቅላላ ዋጋ 20% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ለየቦታ ኮዱ በጋዜጣው ላይ የተቀመጠውን መጠን ማስያዝ ይኖርባቸዋልይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም 20% ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል። እንዲሁም አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡ከአዲስ አበባ ውጪ ከሚገኙ ባንኮች ሲፒኦ ስታሰሩ አዲስ አበባ ከሚገኙ ባንኮች በኔትወረክ የተያያዘ መሆን አለበት ይህ ሳይሆን ቀርቶ ችግር ቢፈጠር /ቤቱ አይጠየቅም።
  6. ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ስትመልሱ፣
    • 6.1 ኦርጅናል ሲፒኦ (CPO)
    • 6.2 ኦርጅናል የመስሪያ ቤቱ ማህተም ያረፈበት የጨረታ መልስ ማቅረቢያዉ ሰነድ
    • 6.3 የተጫራቹ መታወቂያ ኮፒ
    • 6.4 የጨረታ ሰነድ የተገዛበት ደረሰኝ ኮፒ
    • 6.5 ተጫራቹ የሚጫረተው በተወካይ ከሆነ የተወካይ መታወቂያ እና የውክልና ማስረጃ ኮፒ
    • 6.6 ተጫራቹ የውጭ አገር ዜግነት በትውልድ /ያዊ የሆነ በሚኖርበት አገር ከሚገኝ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ወይም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጠ እና በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ /ቤት የፀደቀ መታወቅያ ኮፒ
    • 6.7 የንግድ ማህበራት ለሆኑት በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ /ቤት የፀደቀ የማህበሩን መመስረቻ ፅሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ ሌሎች ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች ከሆኑ ህጋዊነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ እና የታደሰ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ
    • 6.8 ጨረታው የሚሳተፉት ባልና ሚስት በአንድ ሰነድ ከሆነ ህጋዊ የጋብቻ ማስረጃ ኮፒ
    •  6.9 በአንድ የጨረታ ሰነድ ከአንድ ሰው በላይ ሆነው ለመወዳደር ከፈለጉ ከሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ /ቤት የተረጋገጠ የተደራጁበትን ህጋዊ ማስረጃ ኮፒ በፖስታ በማሸግ የጨረታ ቁጥር እና የቦታ መለያ ኮድ በመፃፍ ግንቦት 23 ቀን 2015 . ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቢሮ ቁጥር 101 (ለም ሆቴል አካባቢ ኤም ህንፃ ላይ) ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 24 ቀን 2015 . ከጠዋቱ 3 00 ሰዓት ጀምሮ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በቦሌ /ከተማ አስተደዳር አዳራሽ የሚከፈት ሆኖ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል። ተጫራቾች ቦታውን በአካል ለመመልክት ከፈለጉ 14/9/15 . ም፣16/09/15 . እና 18/09/15 . ጠዋቱ 3 00 እና ከሰዓት 8 ሰዓት ለጨረታ የተዘጋጁ ቦታዎች የሚገኙበት /ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር /ቤት ድረስ በመቅረብ ለዚህ ስራ በሚመደቡ አስጎብኝዎች አማካኝነት ቦታዎቹን መመልከት ይቻላል።
  8. በጨረታዉ ተሳትፋችሁ ተሸናፊ የሆናችሁ ተጫራቾች ያስያችሁት የጨረታ ማስከበሪያ .. (CPO) ተመላሽ የሚደረገዉ የጨረታ ዉጤት በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከተገለጸ ጀምሮ ተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ባለቤቱ ወይም ህጋዊ ወኪሉ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያና የዉክልና ማስረጃ እንዲሁም የሲ.. (CPO) ቀሪ በመያዝ መዉሰድ የሚቻል መሆኑን እየገለጽን ከዚህ ዉጭ የሚመጡ ደንበኞችን የማናስተናግድ መሆኑን በቅድሚያ እንገልጻለን።
  9. መስሪያ ቤቱ (ቢሮው) የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፦

በስልክ ቁጥር +251 11 156 6440 መረጃ ማግኘት ይቻላል።

https://addismayor.gov.et/  

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ




___________________________________________________________________________________
Category : Land and Lease, Sale.
Posted Date : 2023-05-24 07:52:35
Deadline :
2023-06-07 (Bid Closed.)

 
   

Copyright © 2011 - 2024 Habesha Tender
Telephone: +251-118-961881/ +251-911-891169 / +251-920-105191, P.O.Box: 122841
Office Address: Aberus Complex 4th floor, office No 405, Bole Road infront of Dembel City Center
Email: contact@habeshatender.com || Website: www.habeshatender.com